አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ10ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል በሜዳው ኢምሬትስ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሃል ሲቲን ያስተናግዳል፡፡
የሊጉ መሪ አርሰናል በሊጉ አምስተኛ ተከታታይ ድሉን ለማሳካት ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
አርሰናል የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ማንቼስተር ሲቲ እስኪጫወት ድረስ የነጥብ ልዩነት ወደ 6 ከፍ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
በሊጉ ያለፉትን 7 ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለው ሃል ሲቲ ወደ ድል ለመመለስ የሚያደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች በሁሉም ውድድር እርስበርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች አርሰናል አራቱን ሲያሸንፍ፤ በአንዱ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ምሽት 2 ሰዓት 30 ላይ ማንቼስተር ሲቲ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
በሊጉ ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች የተሸነፈው ማንቼስተር ሲቲ ወደ ድል ለመመለስ ይፋለማል፡፡
ያለፉትን አምስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለው ኖቲንግሃም ፎረስት ወደ አሸናፊነት ለመምጣት የሚያደርገው ፉክክር ይጠበቃል፡፡
በሌላ የሊጉ ጨዋታዎች ቀን 9 ሰዓት 30 ላይ ሊድስ ዩናይትድ ከቶተንሃም ሆትስፐር እንዲሁም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ፉልሃም ከኒውካስል ዩናይትድ ይገናኛሉ፡፡

