Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የክልሉን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አስጀምረዋል፡፡

ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በተገኙበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2019 የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በጋሞ ዞን ተካሂዷል።

የማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ “የውሃ ጸጋችንን አሟጠን በመጠቀም ከዝናብ ጥገኝነት የተላቀቀ ግብርናን እውን ለማድረግ እንሠራለን” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሉሲ እርሻ ልማት ድርጅት እየለማ የሚገኝ የማንጎ ማሳን መጎብኝታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

Exit mobile version