Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ማንቼስተር ሲቲ በኖቲንግሃም ፎረስት 3 ለ 1 ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ10ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲን ኖቲንግሃም ፎረሰት 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ይህን ተከትሎ ማንቼስተር ሲቲ ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈት ገጥሞት ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ 6 ከፍ ብሏል፡፡

ሃየር ኩንሃ በ6ኛው ደቂቃ እንዲሁም ሊያም ዴላፕ በ18ኛው እና በ73ኛው ደቂቃ የኖቲንግሃም ፎረስትን ግቦች ሲያስቆጥሩ ለማንቼስተር ሲቲ ራያን ቸርኪ 52ኛው ደቂቃ ላይ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ቀደም ሲል በተካሄዱ ጨዋታዎች የሊጉ መሪ አርሰናል ሃል ሲቲን እንዲሁም ሊድስ ዩናይትድ ቶተንሃምን በተመሳሳይ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲሸንፉ  ፉልሃም ከኒው ካስትል 1 ለ 1 ተለያይተዋል፡፡

Exit mobile version