Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዛሬ ጨዋታዎች

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 29፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ10ኛ ሳምንት እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ቀን ውሎ ዛሬ ምሽት 5 ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

በመርሃ ግብሩ ምሽት 11 ሰዓት አራት ጨዋታዎች ሲደረጉ ቼልሲ ከሰንደርላንድ እንዲሁም ሊቨርፑል ከክሪስታል ፓላስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት ብራይተን ከብረንትፎርድ እንዲሁም ኢፕስፒች ከቦርንማውዝ ጨዋታቸውን ያደርጋሉለ።

ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ደግሞ በኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንቼሰተር ዩናይትድ አስቶንቪላን ያስተናግዳል፡፡

ሊጉን አርሰናል በ27 ነጥብ ሲመራ ማንቼስተር ሲቲ በ21 እንዲሁም ብራይተን በ19 ነጥብ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

Exit mobile version