አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልፅግና ፓርቲ የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የፓርቲው ዋና ጽ/ቤትና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በግምገማው ላይ የሩብ ዓመቱ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ የገጠሙ ተግዳሮቶችና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት የቀጣይ የሥራ አፈጻጸምን ለማጠናከር ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
የአፈጻጸም ክፍተቶችን ማረምና ቀጣይ ሥራዎችን በተሻለ ውጤታማነት ለመፈጸም በሚያስችሉ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት መደረጉንም የፓርቲው መረጃ ያመለክታል፡፡

