Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 584 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 584 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ወደ ሀገራቸው የተመለሱት 1ሺህ 432 ወንዶች፣ 131 ሴቶች እና 21 ህፃናት ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 25ቱ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።
ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራም እየተሰራ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሥራ እስካሁን ከ114 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
Exit mobile version