አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ በቱርኪዬ አንታሊያ መካሄድ በጀመረው ኮፕ- 31 የኢትዮጵያ ፓቪሊዮን በይፋ ተከፈተ፡፡
የኢትዮጵያ ፓቪሊዮን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ- 32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፣ በፋይናንስ ሚኒስትርና የኮፕ- 32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ነው በይፋ የተከፈተው፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ ዲፕሎማቶች፣ የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን አባላት፣ የአጋር ድርጅቶች ተወካዮች እና ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም ሌሎች ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

