Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በ4ኛው ወጣቶች ኦሊምፒክ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለአሸናፊነት ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2019 9 (ኤፍ ኤም ሲ) በ4ኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ በዛሬው ዕለት በሚካሄዱ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለአሸናፊነት ይጠበቃሉ።
ቀን 11 ሰዓት በወንዶች 2 ሺህ ሜትር መሰናክል ፍጻሜ አትሌት ጁነዲን አብዶ ይወዳደራል።
በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል 8:22፡33 የግል ምርጥ ሰዓት ያለው አትሌቱ ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚሆን ይጠበቃል።
አመሻሽ 12 ሰዓት ከ03 ላይ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር ፍጻሜ የምትወዳደረው አትሌት ዮርዳኖስ ጽጋብ ደግሞ በአምስት ወራት ውስጥ ለኢትዮጵያ ሦስተኛ የወርቅ ሜዳሊያ ለማስገኘት ወደ ሜዳ ትገባለች።
አትሌት ዮርዳኖስ በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው 2ኛው የአፍሪካ ዞን 5 የወጣቶች ኦሊምፒክ በ3 ሺህ ሜትር ውድድር እንዲሁም በዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በ3 ሺህ ሜትር ለሃገሯ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ማስገኘቷ ይታወቃል።
ምሽት 1 ሰዓት ከ26 ላይ ደግሞ በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ፍጻሜ አትሌት ዋቢ ወጂራ የሚወዳደር ሲሆን አትሌቱ በናይሮቢ በተካሄደው 2ኛው የአፍሪካ ዞን 5 የወጣቶች ኦሊምፒክ በ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር ለሀገሩ የብር ሜዳሊያ ማስገኘቱ ይታወሳል።
ምሽት 1 ሰዓት ላይ ደግሞ በወንዶች 800 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ አትሌት ዮሚፍ አበበ ወደ ፍጻሜው ለማለፍ የሚወዳደር ሲሆን ምሽት 2 ሰዓት ከ10 ላይ በሴቶች 800 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ አትሌት ነፃነት ሰለሞን ትወዳደራለች።
የዛሬው ውድድር ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች በወጣቶች ደረጃ ያላቸውን ብቃት በዓለም መድረክ ለማሳየትና ለሀገራቸው ተጨማሪ ሜዳሊያዎችን ለማስገኘት የሚያደርጉት ወሳኝ ፍልሚያ ይሆናል።
Exit mobile version