አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር እና የኮፕ – 32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከP4G (Partnering for Green Growth and the Global Goals) ዋና ዳይሬክተር ሮቢን ማክጉኪን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከኮፕ – 31 ጉባኤ ጎን ለጎን ነው የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጉት፡፡
ውይይታቸውም የአየር ንብረት ፈጠራ ሥርዓቶችን ማጠናከር፣ ለአየር ንብረት ጉዳይ ሥራ ፈጣሪዎች ኢንቨስትመንትን ማሳደግ እና ለዘላቂ ልማትና ለአረንጓዴ ዕድገት የሚያግዙ ተግባራዊ መፍትሔዎችን ማስፋፋት ዙሪያ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
እንዲሁም በየካቲት 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄደውን የP4G ኢትዮጵያ ጉባኤ ወደ COP32 በሚደረገው ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

