አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ከCOP31 ጉባኤ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር በረከት ፍስሃፅዮን ከዓለም አቀፉ የሜትሮሎጂ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ሴሌስቴ ሳውሎ (ፕ/ር) ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅት ሁለቱ ወገኖች በአየር ንብረትና አየር ሁኔታ ምልከታ ሥርዓቶች ላይ ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
እንዲሁም የቅድመ ማስጠንቀቂያ አቅሞችን ማሳደግና የአየር ንብረት መረጃዎችን ፍትሃዊ ተደራሽነት ማበረታታት በሚቻልባቸው ነጥቦች ላይም ተወያይተዋል።
በአዲስ አበባ ከሚካሄደው COP32 ጉባኤ አስቀድሞ በሳይንስ ላይ የተመሰረተ የአየር ንብረት ጥበቃን ማጠናከር በሚቻልበት አቅጣጫ ላይ የተወያዩ ሲሆን፤ በጠንካራ የምልከታ አውታረ መረቦች፣ በመረጃ ፍትሃዊነት፣ በአቅም ግንባታ እና በዓለም አቀፍ ትብብር አማካኝነት የጋራ የመቋቋም አቅምን ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

