አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ከቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ በኮፕ31 የመሪዎች ጉባኤ ዋዜማ በአንታሊያ ቱርክ በመገኘት ከፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ አጋርነት መሠረት በማድረግ የሁለትዮሽ ትብብራችንን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ ተወያይተናል ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኮፕ31 ጉባኤን ለማስተናገድ ለተደረገው ዝግጅትና ጉባኤው በድምቀትና በስኬት እንዲጠናቀቅ ቱርክዬ እያሳየችው ላለው ጥረት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ይህም ኢትዮጵያ የኮፕ32 ፕሬዚዳንትነትን ለመረከብ በምታደርገው ዝግጅት ላይ የሚኖረውን አጋርነት እንዲሁም የጋራ ትኩረት በሚሹ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመተባበር የሚያስችሉ ዕድሎችን ተመልክተናል ብለዋል።
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ #ኮፕ_32_ኢትዮጵያ #fanamediacorporation

