Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከፊንላንድ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፊንላንድ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ከኮፕ31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንደገለጹት፤ ከፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ቀደም ሲል በጂ20 (G20) ጉባኤ ወቅት ባካሄዱት የሁለትዮሽ ስብሰባ ላይ የተደረጉ ውይይቶችን ተግባራዊነት በተመለከተ መምከራቸውን አብራርተዋል።
በተጨማሪም በውይይታቸው ዋና ዋና ዓለም አቀፍ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮችን፣ በቀጣናዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን እና በጋራ ፍላጎቶች ላይ መምከራቸውን አመልክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ውይይቱ ፊንላንድ ኢትዮጵያ የምትረከበውን የኮፕ32 ፕሬዚዳንትነት የምታደርገውን ድጋፍ ጨምሮ በጋራ መግባባት የተደረሰባቸውን ዘርፎች ቀጣይነት ባለው ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ልዩ ትኩረት የተሰጠበት እንደሆነ አስገንዝበዋል።
Exit mobile version