አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)ኢትዮጵያ ዓለም የምትጓዝበትን የቴክኖሎጂ ፍጥነት ከዳር ተመልካችነት ይልቅ በግንባር ቀደምትነት ለመምራትና ለአህጉሪቱም በተምሳሌትነት ለመቆም የሚያስችላትን ጠንካራ መሰረት እየጣለች ትገኛለች፡፡
ከእነዚህም የቴክኖሎጂ መገለጫዎች አንዱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ነው ሲሆን፤ ይህም እስከ ተቋም ግንባታ ድረስ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ተቋም ኢትዮጵያ የምትከተለውን አፍሪካዊ መፍትሔ ለአፍሪካዊ ችግሮች መርህ የሚደግፍ ሲሆን፤ ወጣቶችን በተገቢው መንገድ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ማስተማርና ማብቃት ነው፡፡
ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ የሰነቀችውን ርዕይ ለማሳካት በላቀ ቴክኖሎጂና መሰረተ ልማት ላይ የምታደርገው ኢንቨስትመንት አፍሪካውያን ወጣቶች የራሳቸውን ችግር በራሳቸው የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች እንዲፈቱ በር ይከፍታል።
ኢትዮጵያ የሰውሰራሽ አስተውሎት የሚፈልጋቸውን መሰረተ ልማቶች ለማሟላት እየሰራች የምትገኝ መሆኗ ከሀገር ውስጥ ዜጎች ባሻገር በአህጉሪቱ ለሚገኙ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤቶችና ስታርት አፖች በር የሚከፍት አህጉዊ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ ርምጃ ነው፡፡
የኤአይ ዩኒፖድ ማዕከል በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራምና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የአርቴፊሻ ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ትብብር እንዲሁም በጃፓን መንግሥት ድጋፍ በየካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል፡፡
ማዕከሉ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአህጉሪቱ የእውቀት፣ ልምድና የፈጠራ ስራዎች ሽግግር የሚያግዝ የቴክኖሎጂ ድልድይ ነው፡፡
ይህ የአህጉራዊ አጋርነት ማረጋገጫ የሆነው ማዕከል ላይ ኢትዮጵያ ሚናዋ ትልቅ በመሆኑ ለአህጉራዊ ትብብርና የጋራ እድገት ያላትን ቁርጠኝነት በተጨባጭ ያሳያል፡፡
በዘርፉ የሰዎችን አቅም ለማብቃት የምታደርገው ጥረትም ለሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን፤ መላው አፍሪካን በዲጂታል ዘመን ተወዳዳሪ የሚያደርግና የጋራ የኢኮኖሚ እድገትን የሚያፋጥን ዘላቂ አቅም ይፈጥራል።
ሀገራዊ ድንበርን የተሻገረ ሰፊ ርዕይ ያለውን ጉዞ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አገልግሎት ዘርፍ እያደረገች ሲሆን፤ ይህም አህጉሪቱ በምዕራባውያን የቴክኖሎጂ ጥገኝነት ስር እንዳትወድቅ እና የራሷን የዲጂታል መደገፊያ እንድትገነባ ያስችላታል።
በመሆኑም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የሚደረገው እያንዳንዱ ርምጃ አህጉሪቱን ወደ አዲሱ የዲጂታል ዘመን በጥንካሬ የሚያሸጋግር እና የወደፊቷን አፍሪካ በቴክኖሎጂ የበለጸገች የሚያደርግ ታሪካዊ ጉዞ ነው።
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ
በቤተልሔም ግርማ

