Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶችን ጨምሮ የከተማዋ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

ውይይቱ በትግራይ ክልል ሰላምና መረጋጋትን ማጠናከር፣ የማኅበረሰቡን ስጋቶችና ጥያቄዎች ማዳመጥ እንዲሁም በጋራ መግባባትና ትብብር የሰላም ግንባታ ሥራዎችን ማስፋፋት ላይ ያተኮረ ነው።

በግዛቸው ግርማዬ

Exit mobile version