Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም ባንክ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም ባንክ ግሩፕ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ዛሬ ከባንኩ ጋር ያለንን የረጅም ጊዜ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ያለመ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

እስካሁን በከተማ የውሃ አቅርቦት መሠረተ ልማት ማስፋፊያና ማሻሻያ፣ በፍሳሽ መሰብሰቢያና ማጣሪያ ተቋማት ግንባታ፣ እንዲሁም በትራንስፖርትና በሌሎች ቁልፍ የልማት ዘርፎች ከዓለም ባንክ ግሩፕ ለተገኘው ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን ነው ያሉት።

በቀጣይም የከተማ አስተዳደሩ ከባንኩ ጋር ያለውን ትብብር በማስፋት፣ አዳዲስ የጋራ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና በመተግበር ለከተማዋ ዘላቂ ልማትና ለዜጎች የተሻለ ኑሮ በጋራ ለመሥራት ጥሩ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

Exit mobile version