አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግሥታት ልዑካንና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በመቐለ ከተማ ከሚገኙ የሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት አካሂደዋል።
ልዑካኑ ከትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር አመራሮች ጋር ውይይት ካካሄዱ በኋላ ከሃይማኖት አባቶቹ ጋር የተወያዩ ሲሆን፣ ውይይቱ በክልሉ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታና የተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮችን የተመለከተ ነበር።
ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በመቐለ ከተማ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያካሄዱ የሚገኙት ልዑካኑ፣ በቆይታቸው ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር እንደሚወያዩ ተመላክቷል።
ጉብኝቱ በክልሉ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለመረዳትና በክልሉ ባሉ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ያለመ እንደሆነም ነው የተገለጸው።
በግዛቸው ግርማዬ

