አቶ ሞቱማ መቃሳ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ባላት መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ፣ በታሪክም ሆነ በሕግ የባሕር በር ባለቤትነቷን የማረጋገጥ መብት አላት።
ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋ በማደግ ላይ የሚገኝ ትልቅ ሀገር በመሆኗ ይህ ዕድገት ታፍኖ ሊቀጥል እንደማይችል ገልጸው፤ ከቀይ ባሕር በጣም በቅርብ ርቀት ላይ መገኘቷ ጉዳዩን ተግባራዊ እንደሚያደርገው አመልክተዋል።
በታሪክ የኢትዮጵያ የነበረው የባሕር በር ባለቤትነት መመለስ ያለበት የሕልውና ጉዳይ በመሆኑ አሁን የተጀመረው ጥረት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
በዓለም አቀፍ ሕግ ኢትዮጵያ ወደቡን የመጠቀም መብቷ የተጠበቀ መሆኑን በመግለጽ፤ ይህም ለቀጣናቂ ሰላምና ደህንነት አስፈላጊ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከኢትዮጵያ ባሻገር ለጋራ ተጠቃሚነት ወሳኝ በመሆኑ፤ የቀጣናው ሀገራት ሊደግፉት ይገባል ነው ያሉት፡፡

