Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስኬት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) 26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከ61 ሺህ በላይ ሰዎችን በማሳተፍ በስኬት ተጠናቅቋል።

26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የመደመር መንግሥት ስፖርትን ሀገራዊ ልማታዊ አጀንዳ ማድረጉን በተግባር ያሳየበት ሆኖ በስኬት መጠናቀቁን የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የኢትዮጵያን የስፖርት አቅምና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት በደማቁ ያሳየበትም ሁነት መሆኑንም ጠቁሟል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለና እያደገ የመጣው ይህ ታላቅ የጎዳና ላይ ሩጫ፣ የዘንድሮው መርሐ ግብር ከምንጊዜውም በላይ ደረጃውን ጠብቆ እንዲካሄድ የመደመር መንግሥት ለስፖርቱ ዘርፍ የሰጠው ልዩ ትኩረትና ሁለንተናዊ ድጋፍ ከፍተኛውን ድርሻ ተወጥቷል ብሏል።

መንግሥት የስፖርት ዘርፉን ለማዘመንና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ውድድሮችን ለማስተናገድ የዘረጋው አሠራር ውድድሩ የሀገሪቱን ገጽታ በሚገነባና የስፖርት ቱሪዝምን በሚያነቃቃ መልኩ እንዲጠናቀቅ ማስቻሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

Exit mobile version