Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ እና ስሎቫኪያ በሰላማዊ የኒውክሌር ኃይል ልማት ትብብር ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ኮሚሽነር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከስሎቫኪያ አምባሳደር ራስቲስላቭ ክሪዣን ጋር ተወያይተዋል።
ኮሚሽነሩ በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን ፈጣን የኢንዱስትሪና የኢኮኖሚ ዕድገት ለመደገፍ የኃይል ምንጮቿን ማስፋፋትና የኒውክሌር ኃይልን በሀገሪቱ የኃይል ሥርዓት ውስጥ ማካተት ያለውን ስትራቴጂያዊ ፋይዳ አብራርተዋል።
አምባሳደር ራስቲስላቭ ክሪዣን በበኩላቸው ስሎቫኪያ በኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ቴክኖሎጂ፣ በኒውክሌር ደኅንነት አጠባበቅና በዘርፉ የረጅም ጊዜ አስተዳደር ያካበተችውን ልምድ አንስተዋል።
ሁለቱ ወገኖች በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሰው ኃይል አቅም ግንባታና ሥልጠና፣ እንዲሁም በኒውክሌር መሠረተ ልማት በጋራ ሊሠሩባቸው በሚችሉ ጉዳዮች ላይ መክረው፣ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር መግባባት ላይ ደርሰዋል።
Exit mobile version