Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመቐለ ሁሉም አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ እንዲያገኙ ተመቻችቷል – የክልሉ ንግድ ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በመቐለ ከተማ ሁሉም የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ እንዲያገኙ ተመቻችችቷል አለ የትግራይ ክልል ንግድ ቢሮ።

የክልሉ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋይ ግርማይ እንዳሉት፤ በከተማዋ 750 ታክሲዎች በልዩነት በተመደቡ ማደያዎች ነዳጅ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው።

ፈቃድ ካገኙ 15 የከተማዋ የነዳጅ ማደያዎች ውስጥ 12ቱ ነዳጅ ከጅቡቲ በማስገባት ማከፋፈል መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

የነዳጅ ግብይቱን ከሕገወጥ ሰንሰለት ለመታደግ በነዳጅ ማደያዎች ላይ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ የነዳጅ አቅራቢዎቹ በዲጂታል የክፍያ አማራጭ ብቻ ክፍያ መፈጸም እንዲችሉ መደረጉንም ጠቁመዋል።

ማደያዎች ለተቋማት እና ለአገልግሎት ሰጪዎች በሴክተር ተከፋፍለው ነዳጅ እንዲያቀርቡ መደረጉን ገልጸው፤ ይህም የሚቀርበው ነዳጅ ላልተፈለገ ዓላማ እንዳይውል ያደርጋል ብለዋል።

በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎቹ የሚገኙ 75 ማደያዎች ላይ ፍተሻና ማጣራት በማድረግ ነዳጅ ማስገባት እንዲችሉ ፈቃድ መሰጠቱንም ኃላፊው ተናግረዋል።

በሚቀጥለው ሳምንት ወደክልሉ የተለያዩ ዞኖች ነዳጅ መግባት እንደሚጀምርም አረጋግጠዋል።

በአሸናፊ ሽብሩ

Exit mobile version