Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተገኙበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2019  (ኤፍ ኤም ሲ) 7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መንግሥት በቀጣይ ትኩረት የሚያደርግባቸውን ዋና ዋና አቅጣጫዎች እንዲሁም በአዲሱ በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ሥራዎችንና የተገኙ ውጤቶችን ያብራራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግሥትን አቋም ካቀረቡ በኋላ፣ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበውን የድጋፍ ሞሽን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

Exit mobile version