Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በ7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

የዓለም አሁን ያለው የፖለቲካ ውጥረት፣ ንትርክ፣ ግጭት እና ውድድር በርካታ ችግሮችን ያስከተለ ቢሆንም በዋናነት ግን የንግድ ስርዓትን አዛብቷል፡፡ የተዛባው የንግድ ስርዓት በዓለም ላይ የሚጨበጥ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደር ችሏል፡:
አንደኛው ችግር የንግድ መስመሮች መታወክ ነው አንድ ሀገር፣ አንድ ኩባንያ፣ አንድ ግለሰብ ከአንድ ስፍራ እቃ ገዝቶ ለእሱ የስራ ግብዓት ይውላል ብሎ ባሰበበት ቀን እና እቅድ መፈፀም አይችልም፤ ከቻይና የተነሳው መርከብ ሌላ ሀገር ቆሟል ሊባል ይችላል። በመንገድ ላይ ባለው መስተጓጎል ምክንያት በርካታ የንግድ ሂደቶች እና ስርዓቶች ታውከዋል፡፡
ዋና ዋና የሚባሉ ምርቶች ምርቶች ለምሳሌ ነዳጅ እና ማዳበሪያ ከፍተኛ የሆነ የምርት እጥረት አጋጥሟል፤ እነዚህን የሚያመርቱ ሀገራት እና ኩባንያዎች በደረሰባቸው ልዩ ልዩ ጫናዎች የምርት እጥረት አጋጥሟል፡፡
የምርት እጥረት እንደሚያጋጥም አውቀው አስቀድመው የሚያግበሰብሱ ሀገራት ሽሚያ ስላበዙ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪዎች አጋጥሟል።
በገበያ ላይ የመገኘት እድል በማነሱ በምርቶቹ ላይ እጥረት ተፈጥሯል፡፡ አሜሪካ እና አውሮፓን ጨምሪ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የኑሮ ውድነት ተፈጥሯል፡፡
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ዓለም ቢበዛ 3 ነጥብ 1 በመቶ ብቻ ልታድግ እንድምትችል ገምቷል፤ ከሰሀራ በታች ያሉ ሀገራት ደግሞ 4 ነጥብ 3 ገደማ ብቻ ሊያድጉ እንደሚችሉ ገምቷል፡፡
ኢትዮጵያ ግን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሲከናወኑ የነበሩ ሪፎርሞች በከፍተኛ ደረጃ ኢኮኖሚያችን ጠንካራ ሆኖ እንደሀገር እንድንፀና አግዘዋል፡፡
በእመቤት ሲሳይ
Exit mobile version