በ7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡- mihret demissie 16 minutes ago ከለውጡ በኋላ እድገት ካስመዘገቡ ዘርፎች መካከል ማኑፋክቸሪንግ አንዱ ነው፤ በቀደመው ጊዜ ያንን እድገት በበቂ ሁኔታ የሚለካ ስርአት አልነበረም፡፡ አረንጓዴ ዐሻራ ዛፍ መትከል ብቻ ሳይሆን በፍራፍሬ እና በቡና ረገድ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ እያስመዘገበ የሚገኘውን እድገት የሚታወቅ ቢሆንም ኢኮኖሚው ያንን ከልሶ ያቀፈ አልነበረም። በኃይል ዘርፍ በንፋስ የአሰላ እና የአይሻ የኃይል ማመንጫዎች ተመርቀዋል፤ ከግድብ አንጻር ገናሌ ዳዋ እና ህዳሴ ተመርቀዋል፤ ከሶላር አንጻር በርከት ባሉ የገጠር ኮሪደር ልማት እየተገነባ ይገኛል። ከቱሪዝም አንጻር ባለፉት ዓመታት በርካታ መሰረተ ልማቶች ተገንብተዋል፤ ውጤትም እየታየበት ይገኛል፡፡ ከቀናት በፊት በአዲስ አባባ ሁለት ኮንፍረንሶች በተመሳሳይ ጊዜ ተካሂደዋል፤ በዚህም ከ35 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡ የባቡር ኮርፖሬሽን ከዓመታት በፊት በመንግሥት የሚተዳደር አልነበረም፤ የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር ኮርፖሬሽንን ለማሻሻል በተከናወኑ ስራዎች ከዚህ በፊት ይገኝ የነበረውን ትርፍ ከ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ወደ 43 ቢሊየን ብር ማሳደግ ተችሏል። 11 የነበሩት ሎኮሞቲቮች 36 ደርሰዋል፣ አሁን ላይ 560 የነበሩት ጋሪዎች በማሳደግ ከ1 ሺህ በላይ ጋሪዎችንም ማስተዳደር ችሏል። የመንገደኞችን አገልግሎትም ከ198 ሺህ ወደ 588 ሺህ አሳድጓል፤ ከጋርጎ አንጻርም ወደ 4 ነጥብ 3 ሚሊየን ቶን ካርጎ ማሳደግ ተችሏል። የባቡር የማጓጓዝ ፍጥነት ከ37 ኪሎ ሜትር በሰዓት ወደ 55 ኪሎ ሜትር አድጓል፡፡ ከ95 በመቶ ያላነሰ የቡና ወጪ ንግድ እንዲሁም 25 በመቶ የማዳበሪያ ገቢ ንግድም በባቡር እየተከናወነ ነው፤ አሁን ላይ ወደ 100 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ስራዎችን በራስ አቅም እየገነባን ነው። #ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ በምሕረት ደምሴ