Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመቐለ ከተማ ለሁሉም አይነት ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በመቐለ ከተማ ለሁሉም የኮድ 2 እና የኮድ 3 ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ለባለሶስት እግር እና ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች ነዳጅ መቅረብ ጀምሯል።

በከተማዋ ባለፉት ቀናት ለታክሲ የሕዝብ አገልግት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ እንዲቀርብላቸው ተደርጓል።

አሁን ላይ ደግሞ በከተማዋ በሚገኙ ሁሉም የኮድ 2 እና የኮድ 3 ተሽከርካሪዎች በማንኛውም ሰዓት ነዳጅ ማግኘት የሚችሉበት አሰራር ተጀምሯል።

ከዚህ በተጨማሪ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጅ እና ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ቤንዚል እንዲያገኙ ተፈቅዷል።

የነዳጅ ማደያዎቹ ወደ መደበኛ ሥራ መመለሳቸው የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ከማቀላጠፍ ባለፈ የሚስተዋሉ ሕገወጥ አሠራሮችን ለመቆጣጠር ወሳኝ ሚና አለው።

በአሸናፊ ሽብሩ

Exit mobile version