Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሴት ተማሪዎችን ስኬት ያስቀጠለችው ዶ/ር እጹብ ስንታየሁ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሴት ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብን ባህላቸው እያደረጉት መጥተዋል።
በዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዘንድሮ የህክምና ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት በዶ/ር እጹብ ስንታየሁ ተመዝግቧል።
ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበችው ዶ/ር እጹብ ስንታየሁ 3.86 ያመጣች ሲሆን አንደኛ ደረጃን ይዛለች።
ባለፈው ዓመት የዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከፍተኛው ውጤት በሴት ተማሪ መመዝገቡን ያስታወሰው የዩኒቨርሲቲው መረጃ፤ በዘንድሮ ምሩቃን ከተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ሶስተኛው በሴት ተማሪ መመዝገቡን ገልጿል።
ዶ/ር ቃልኪዳን ላቀው 3.73 ውጤት በማስመዝገብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች።
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ግርማው አሸብር ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ የዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በነገው እለት 92 ሀኪሞችን ያስመርቃል።
ከተመራቂ ሀኪሞች መካከል 36ቱ ሴቶች መሆናቸውን ገልጸው፤ ሴት ተማሪዎቹ በከፍተኛ ትጋት ስኬት እያስመዘገቡ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡
በትዕግስት ግዛቸው
Exit mobile version