አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለአደራ ምክር ቤቱ ታቅደዉ የተሰጡትን ሥራዎች በታቀደላቸው ጊዜ ለመስራት እየተንቀሳቀሰ ነው አሉ የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የኢኮኖሚና መልሶ ግንባታ ዋና አስፈጻሚ ቴዎድሮስ አረጋይ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ጋር የግምገማ ውይይት አካሂደዋል።
ውይይቱን አስመልክቶ የክልሉ ባለአደራ አስተፋፈር የኢኮኖሚና መልሶ ግንባታ ዋና አስፈጻሚ ቴዎድሮስ አረጋይ (ዶ/ር) በሰጡት አስተያየት እንዳሉት፤ እስካሁን በዞን እና በወረዳዎች አመራሮችን የመመደብ እና የአስተዳደር ሥራዎች የመመለስ ተግባራት ተከናውነዋል።
የወደሙ ቢሮዎችን እና የሥራ ቦታዎችን መካከለኛ ጥገና በማድረግ ተቋርጠው የነበሩ የመንግስት አገልግሎቶች እንዲጀመሩ መደረጉንም አብራርተዋል፡፡
ከሰላም እና ፀጥታ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ስጋቶች እንደነበሩ አንስተው በሂደት ስጋቶቹ እንዲቀንሱ እና ህዝቡም ያለ ምንም ስጋት ተንቀሳቅሶ እንዲሰራ ለማድረግ ሰፊ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
ተቋርጠው የነበሩ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲነቃቁ በማድረግ የነዳጅ ማደያዎች ሥራ እንዲጀምሩ እና ነዳጅ ወደ ክልሉ እንዲገባ መደረጉንም ጠቁመልዋል።
በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች እርዳታ እንዲደርስ እና እንዲቀጥል እየተደረገ መሆኑንም ነው ያነትሱ።
በቀጣይ ደግሞ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው የሚመለሱበት፣ እርዳታዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚገባ አመልክተዋል።
የክልሉ ሰላም እንዲሻሻል ከፍተኛ ሥራዎች ይጠበቅብናል ህዝብን በሁሉም ዘርፍ በማሳተፍ በጋራ እንሰራለን ነው ያሉት፡፡
በእመቤት ሲሳይ

