Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቻይና የነሃሴ ወር የወጪ ንግዷ 9 ነጥብ 5 በመቶ አደገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና የነሃሴ ወር የወጪ ንግዷ 9 ነጥብ 5 በመቶ ማደጉን አስታወቀች።

እድገቱ ለሶስት ተከታታይ ወራት መመዝገቡን ከሀገሪቱ የሚወጡ መራጃዎች ያመለክታሉ።

በአንጻሩ ወደ ውጭ የሚላከው ምርት እድገት እያሳየ ቢሄድም ወደ አገር ውስጥ የሚገባው ምርት በ2 ነጥብ 1 በመቶ ማሽቆልቆሉን ነው የተነገረው።

ከዓመት በፊት የኢኮኖሚ ተንታኞች ወደ አገር ውስጥ የምታስገባው ምርት በ 0 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት እንደሚያሳይ ተንብየው ነበር።

ሆኖም አሁን ላይ በጥቅሉ በ1 ነጥብ 4 በመቶ ማሽቆልቆሉ ነው የተሰማው፡፡

ቻይና ወደ አገር ውስጥ የምታስገባው ምርት ቢቀንስም ሁለተኛው ትልቁ ትርፍ ያስመዘገበችበት ወር መሆኑን ይፋ አድርጋለች።

ባለፉት ስምንት ወራት ከእስያ ሀገራትና ከአውሮፓ ህብረት የምታደርገው የንግድ ልውውጥ እያደገ መሄዱን ገልጻለች።

በአንጻሩ በሦስተኛ ደረጃ ከተቀመጠችው ከንግድ አጋሯ አሜሪካ ጋር ያላት የንግድ ልውውጥ በ0 ነጥብ 4 በመቶ ማሽቆልቆሉ ነው የተነገረው።

ምንጭ፦ሲ.ሲ.ቲቪ

Exit mobile version