አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዋናው መስሪያ ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ አምባሳደሮች እና ቆንስል ጀኔራሎች ዓመታዊ ስብሰባ ተጠናቀቀ።
ስብሰባው “ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኳችን ለሃገራዊ ብልጽግናችን” በሚል መሪ ቃል ነበር ላለፉት 15 ተከታታይ ቀናት በቢሾፍቱ ሲካሄድ የቆየው፡፡
ተሳታፊዎቹ በተያዘው በጀት ዓመት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሚከያናውናቸው ዋነኛ ጉዳዮች ላይ አተኩረው ተወያይተዋል፡፡
እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በአዲሱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ መክረዋል፡፡
በተመሳሳይ በኢትዮጰያ የ10 ዓመት /ከ2013 እስከ 2022 ዓም/ መሪ የልማት እቅድ ላይ ውይይት አድርጓል።
በመጨረሻም የውይይቱ ተሳታፊዎች ባለፉት ሁለት ሳምንታት የመከሩባቸውን ጉዳዮች መሰረት አድርገው ለሀገራቸው የተሻለ ነገር እንደሚያበርክቱ ገልጸዋል፡፡

