Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ 100 ለሚሆኑ አይነስውራን ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት 100 ለሚሆኑ አይነስውራን ማዕድ አጋሩ።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ የማዕድ ማጋራት ስነስርዓቱን ያካሄዱት በዛሬው እለት ነው፡፡

በዛሬው ዕለት በተከናወነው በዚህ ማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ለአይነስውራኑ ሩዝ፣ ዘይት እና ዱቄት አበርክተዋል።

የቀዳማዊ እመቤት ፅህፈት ቤት ችግረኛ አረጋዊያንን፣ አካል ጉዳተኞችንና ሌሎችንም ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ ይታወቃል።

ፅህፈት ቤቱ የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋት በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን በማሰራት የድርሻውን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version