Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በከተማ ደረጃ የብሩህ ተስፋ ቀን በመከበር ላይ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አምስቱን የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ መርሃ ግብሮች ማክበሩን ዛሬም ቀጥሏል ፡፡

በዚህም ዛሬ የብሩህ ተስፋ ቀን በሚል መሪ ቃል ቀኑ እየተከበረ ሲሆን ÷ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የቢጫ ታክሲ አሽከርካሪዎች ትርዒት ሲያሳዩ አርፍደዋል፡፡

ከትርዒቱ ጎን ለጎንም ቀኑን ሚገልፁ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡

መርሃ ግብሩ ቀጥሎ የሚውል ሲሆን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቅርቡ ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ የጠቃጠሉ 30 የሚሆኑ ቤቶች እና ሱቆችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በቅርቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲ.ኤም.ሲ አሊታድ ሚካኤል የደረሰው የእሳት አደጋ 12 ሚሊየን ብር የሚገመት 18 የንግድ ሱቆች ፣11 መጋዘኖች እና አንድ ባርና ሬስቶራንት ላይ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል፡፡

በፍሬህይወት ሰፊው

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version