Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከወር በፊት ፍንዳታ በተከሰተባት የቤሩት ከተማ እሳት መነሳቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) ከወር በፊት ፍንዳታ በተከሰተባትና ከ190 በላይ ሰዎች ለህልፈት በተዳረጉባት የቤሩት የወደብ ከተማ እሳት ተነስቷል።

እሳቱ የተነሳው በከተማዋ የነዳጅና የጎማ እቃ ቤት ላይ ሲሆን÷ በዚህም በከተማዋ የእሳቱ ጭስ ወደ ሰማይ ሲወጣ መታየቱ ተገልጿል።

ነገር ግን ለእሳቱ መነሻ የሆነው ምክንያት እስካሁን አልተገለጸም።

እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል በቦታው ላይ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና የሀገሪቱ የጦር ሂሊኮፍተሮች ውሃ ሲረጩ ታይተዋል።

የሊባኖስ የቀይመስቀል ኃላፊ ጎርጅ ኬታነህ÷ በእሳቱ ጭስ ምክንያት ለመተንፈስ የተቸገሩ ሰዎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።

ነገር ግን ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ስለመኖራቸው ሪፖርት አለመኖሩን ጠቁመው÷በእሳቱ ምክንያት የሚከሰት ሌላ የፍንዳታ ስጋት የለም ሲሉም ተናግረዋል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version