Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት መጀመር በሚቻልበት ላይ የምክክር ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 11 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚመክር ጉባኤ በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2012 የስራ ዘመን ኮሮናን ለመከላከል ያከናወኗቸው አበይት ተግባራትና ያስገኙት ውጤት ይገመገማል።

ትናንት በተጀመረው በዚሁ ጉባኤ የዘንድሮ ትምህርት በሚጀመርበት ሁኔታ ላይ ጉባኤው እንደሚመክርና መረሃ ግብሩ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

ከጉባኤው ጎን ለጎን ኮሮናን ለመከላከል በዩኒቨርስቲዎች የተሰሩ የፈጠራ ምርቶችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ በጅማ ዩኒቨርሲቱ ዋናው ግቢ ተከፍቷል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምርምር፣ በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ያከናወኗቸውን አበይት ተግባራት ይዘው መቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል ።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version