አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ በሚገኘው ኢፌል ማማ (ታወር) ላይ የቦንብ ጥቃት ሊፈፀም ይችላል የሚል የስልክ መልዕክት ለፓሊስ መድረሱን ተከትሎ አካባቢው እንዲዘጋ ተደረገ።
በፖሊስ ተሽከርካሪዎች እና በመንገድ መዝጊያዎች በኢፌል ታወር በታች የሚገኙ አካባቢዎች እና ከሴን ወንዝ ወደ ትሮካዴሮ ፕላዛ የተዘረጋው ድልድይም መዘጋቱ ተነግሯል።
በአካባቢው የተሰማሩ የፖሊስ አባላት በኢፌል ታወር የሚገኙ አካባቢዎች እንዲዘጉ የተደረጉት የቦንብ ጥቃት ሊፈፀም ይችላል የሚል የስልክ መልዕክት ለፖሊስ በመድረሱ መሆኑን መናገራቸውን ኤ ቢ ሲ ዘግቧል።
133 ዓመታትን ያስቆጠረው የአለማችን ረጅሙ ማማ በየቀኑ ከ25 ሺህ በላይ ቱሪስቶች የሚጎበኙት የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት የጎብኚዎች ቁጥር ቀንሷል።

