Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ም/ከ አዳነች አቤቤ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ግንባታ ላይ ለተሳተፉ አካላት የምስጋና የእራት ግብዣ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 14 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ግንባታ ላይ ለተሳተፉ አካላት የምስጋና የእራት ግብዣ አድርገዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የጀመራቸውን ስራዎች በሰዓቱ እንደሚጨርስ ማሳያ የሆነው የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው ለመሩ ፣ ላስተባበሩ እንዲሁም የግንባታው ሂደት ላይ ለተሳተፉ አካላት ነው የምስጋና የእራት ግብዣ የተደረገው።

የፕሮጀክቱ ግንባታ ሂደት ለሌሎች ፕሮጀክቶች ልምድ እና ተሞክሮ የሚሆን ነው ያሉት ምክትል ከንቲባ አዳነች ÷ በተለየ ፍጥነት እና ብርታት ፕሮጀክቱ በተባለው ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ላስቻሉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የፕሮጀክቱ ቀሪ የማጠናቀቂያ ስራዎችም በተጀመረው ፍጥነት እና ጥራት እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን ጽኑ እምነት ገልጸዋል ።

በምስጋና የእራት ግብዣ መርሃ ግብሩ ላይ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ አቶ ጃንጥራር አባይ ፣ የፕሮጀክቱ አስፈጻሚ አካላት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በፕሮጀክቱ ላይ በተለያየ ሙያ የተሳተፉ የግንባታ ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክተሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version