Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

46 ኩንታል ሃሽሽ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 46 ኩንታል ሃሽሽ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

በቁጥጥር ስር የዋለው ተሸከርካሪ መነሻውን ሻሸመኔ በማድረግ ወደ ሁመራ በመጓዝ ላይ ነበር ተብሏል፡፡

ሆኖም ኬላ ሲዘጋበት ወደ መተማ አቅጣጫ ሲጓዝ በአካባቢው የፀጥታ አካል በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተሸከርካሪው ሃሽሹን ሲያጓጓዝ የነበረው 20 ኩንታል በቆሎ እና 18 ኩንታል የከብት መኖ ውስጥ በመሸሸግ ነው ተብሏል፡፡

ፖሊስ አንድ ተሳፋሪን ጨምሮ አሽከርካሪውንና ረዳቱን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሷል።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ይህን ህገወጥ ተግባር በመከላከል ለተሳተፋ የአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

የጸጥታ ኃይሉ በሌሎች ህገወጥ እንቅስቃሴዎች ላይም ጠንካራ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የሕብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ማስተላለፉን ከአማራ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘው መረጃ ያመለከታል፡፡

Exit mobile version