Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ ክልል ለወንጪ ሀይቅ የልማት ፕሮጄክት 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ተገባ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በገበታ ለሀገር ጥሪ መሰረት በኦሮሚያ ክልል ለወንጪ ሀይቅ ልማት ፕሮጄክት 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ተገባ፡፡
በትናትናው ዕለት ለወንጪ ሀይቅ የልማት ፕሮጀክት የገቢ ማሰባሰቢያ በአዲስ አበባ ተከናውኗል።
በዚህም በገቢ ማሰባሰቢያው የተሳተፉ ባለሀብቶች 527 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
በተመሳሳይ በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ማለትም 800 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወስነዋል።
በአጠቃላይ ከባለህብቶቹ እና በየደረጃው ከሚገኙ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ቃል ተገብቷል።
ባለሀብቶች ለክልሉ ብሎም ለሀገር ልማት እና እድገት ያደረጉት አስተዋጽኦ የሀገር ባለውለታነታቸውን የሚያሳይ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ
ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ለወንጪ ፕሮጀክት በቢሊየን ብሮች ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገቡት ባለሀብቶቹ በቀጣይም በሀገር የልማት ጥሪ ላይ ለመሳተፍም ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናገረዋል
ወንጪ ሀይቅ ከአዲስ አበባ 150ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከ 3 ሺህ 380 ሜትር ከፍታ ያለው በተራራ የተሸፈነ እና ብርቅዬ አእዋፍ፣ ፍል ውሃና ታሪካዊ ገዳማትን በውስጡ የያዘ የተፈጥሮ መስህብ ነው፡፡
Exit mobile version