Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሞክታር ኡዋኔ የማሊ የሽግግር ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞክታር ኡዋኔ የሽግግር መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ፡፡

ሹመቱ በሃገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ባህ ንዳው የተሰጠ ነው ተብሏል፡፡

ባለፈው ነሃሴ ወር ላይ በማሊ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት መካሄዱ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም ጎረቤት ሃገራት በማሊ ላይ ማዕቀብ ጥለው ቆይተዋል፤ የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመትም የተጣለባትን ማዕቀብ ለማንሳት በር ከፋች ነው ተብሏል፡፡

የ64 ዓመቱ ኡዋኔ ከፈረንጆቹ 1995 እስከ 2002 በተባበሩት መንግስታት የማሊ አምባሳደር እንዲሁም ከ2004 እስከ 2009 ድረስ ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል ፡፡

ከሳምንት በፊት የሃገሪቱ የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር ባህ ንዳው ጊዜያዊ የሽግግር ጊዜ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸው የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

Exit mobile version