Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጋምቤላ ክልል በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጋምቤላ ክልል በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አድርጓል።
በጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የተመራ ልዑክ በአፋር ክልል ጉብኝት ማድረጉ ተነግሯል።
በዚህ ወቅትም በክልሉ ህዝብ እና መንግስት ስም 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በጎርፍ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረጉ ተጠቁሟል።
የተደረገውን ድጋፍም የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ አስረክበዋል።
ከዚህ ቀደም የተለያዩ ክልሎች እና የፌዴራል መንግስት ተቋማት በአፋር ክልል በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።
Exit mobile version