Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አርመንያ የጦር ጀቷ በቱርክ መመታቱን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አርመንያ የጦር ጀቷ በአየር ክልሏ ውስጥ በቱርክ ጀት ተመትቶ መውደቁን አስታወቀች፡፡

ሰሞኑን አርመንያና አዘርባጃን በተራራሟ ናጎርኖ ካራባኽ ክልል ምክንያት ወደ ጦርነት ገብተዋል፡፡

በሦስት ቀናት ውስጥ ንጹኀንን ጨምሮ 100 ሰዎች መሞታቸው ነው የተሰማው፡፡

ጦርነቱ የተነሳበት ክልል በዓለም አቀፍ ደረጃ በአዘርባጃን ይዞታነት የሚታወቅ ሲሆን የአርመንያ ዝርያ ባላቸው ሰዎች እንደሚመራ ተገልጻል፡፡

በሁለቱ አገራት ግጭት ቱርክ አዘርባጅንን እየደገፈች ነው ቢሉም አንካራ ስሞታውን ውድቅ አድርገዋለች፡፡

ግጭቱን ተከትሎ ሌሎች አገራት በቀጥታ እጃቸውን ሊያስገቡ ይችላሉ እየተባለ ይገኛል፡፡

በአርመንያ የጦር ሰፈር ያላት ሩስያ በአስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቅርባለች፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

Exit mobile version