Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ቦታ ጽዳት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 21 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የሆራ ፊንፊኔየኢሬቻ በዓል ታዳሚዎች በዓላቸውን በሚያከብሩበት ስፍራ ዛሬ ጠዋት የጽዳት ዘመቻና የጸረ ተህዋሲያን ርጭት ተካሂዷል።
በዚህ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የከተማ አስተዳደሩ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር እሼቱ ለማ ÷ የበዓሉ ታዳሚዎች ጽዱ በሆነ ቦታ በዓላቸውን እንዲያከብሩ ጽዳቱ ተከናውኗል ብለዋል።
ጽዳቱ የተከናወነው ከከተማው የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ከተለያዩ የኃይማኖት ተቋማት በተውጣጡ ሰዎችነው ያሉት ዶክተር እሼቱ ÷ ይኸም በዓሉ የጋራችን መሆኑን የሚያመላክትና አብሮነትን የሚገጽ ነው ብለዋል።
የከተማው የከንቲባ ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ወይዘሮ አልፊያ የሱፍ በበኩላቸው÷ በዓሉን ስናከብር ለኮቪድ 19 ጥንቃቄ በማድረግ እና አባ ገዳዎች ባስቀመጡት አቅጣጫ ብቻ መሆን አለበት ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጪው ቅዳሜ መስከረም 23 ቀን 2013 ዓ.ም ለሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በርካታ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በማከናወን ላይ  ነው።

በዚህም  የቦታውን ማረጋገጫ ካርታ ለአባ ገዳዎች መስጠት፣ ለበዓሉ አስተባባሪ ወጣቶች የስምሪት አቅጣጫ መስጠት፣ ከአባ ገዳዎች ጋር በመሆን ስለ ኢሬቻ በዓል ምንነትና እሴት ግንዛቤ መስጠት ይገኝበታል ተብሏል ።

ከዚያም ባለፈ ከተለያየ አካባቢ የሚመጡት ታዳሚዎች የሚስተናገዱባቸው ፕሮግራሞችን ማውጣት እንዲሁም በዓሉ የሚከበርበት ቦታ የመጎብኘትና ጽዱ የማድረግ ስራዎችን በመሰራት ላይ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
Exit mobile version