Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የልዩ ተሰጥኦ ልማት ኢንስቲቲዩት በዚህ አመት ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደሚጀምር ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የልዩ ተሰጥኦ ልማት ኢንስቲቲዩት በዚህ አመት ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይጀምራል፡፡

ተቋሙ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ልዩ ተሰጥኦ እና ተውህቦ ያላቸው ተማሪዎች ገብተው የሚማሩበት ነው፡፡

ለተቋሙ የሚሆን የትምህርት ቀረፃ ላይ ግብዓቶችን ለመሰብሰብ ያቀደ ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚገኙ ተማሪዎች እንዲሁም ከመደበኛ የትምህርት ስርዓት ውጭ በግል ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎች የሚማሩበት መሆኑም ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም በልዩ ስርዓተ ትምህርት፣ ልዩ ዝንባሌና ተሰጧቸውን ባገናዘበ ሁኔታ ትምህርት እንዲሰጣቸው የሚደረግበት መሆኑም ተነግሯል።

ኢንስቲቲዩቱ በዚህ አመት የመማር ማስተማር ስራውን የሚጀምር ሲሆን በቀጣይም 1 ሺህ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዳለው ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version