Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከመስከረም 27 እስከ መስከረም 30 ቀን ድረስ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እንደሚካሄድ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከመስከረም 27 እስከ መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አስታወቀ፡፡

የክትባት ዘመቻው በሶማሌ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች፣ ሃረሪ ክልል እንዲሁም በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ 47 ዞኖች 334 ወረዳዎች ይሰጣል ነው ተባለው፡፡

በዚህም ክትባቱ 7 ሚሊየን ለሚሆኑ ህፃናት እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡

በመሆኑም እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ህፃናት ከአሁን በፊት ክትባቱን ቢከተቡም ባይከተቡም አሁን የሚሰጠውን የፖሊዮ ክትባት መውሰድ ይኖርባቸዋል ነው የተባለው፡፡

በሌላ በኩል የካቲት 24 ቀን 2012 ዓ.ም በደቡብ ክልል የተከሰተውን የቢጫ ወባ ወረርሽኝ ተከትሎ በተከሰተበት ወረዳ ክትባቱን ጨምሮ በተሰጠው ምላሽ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ተችሏል ብሏል፡፡

ሆኖም አሁንም ለወረርሽኙ ስጋት የሆኑ መንስኤዎች አሉ ያለው ኢንስቲቲዩቱ በደቡብ ክልል 11 ወረዳዎች እና አንድ የኦሮሚያ አጎራባች ወረዳን ጨምሮ በአጠቃላይ በ12 ወረዳ የሚኖሩ 704 ሺህ ሰዎች ከጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት በመከናነወን ላይ እንደሚገኝ ከኢንስቲቲዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version