Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ባለፉት 24 ሰዓታት 890 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 3 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 916 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 890 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 76 ሺህ 988 ደርሷል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የ 3 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር 1 ሺህ 208 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መረጃ ያመለክታል።

በ24 ሰዓታት ውስጥ 247 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 31 ሺህ 677 ደርሷል።

እንዲሁም 296 ፅኑ ህሙማን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል።

Exit mobile version