Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ስርአት ጉባኤ ሰኞ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣መስከረም 23 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የመክፈቻ ሥነ-ስርአት ጉባኤ ሰኞ ይካሄዳል።

ጉባኤው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳን ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ሰኞ መስከረም 25 ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚገኘው የስብስባ አዳራሽ እንደሚካሄድም ተገልጿል።

በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ታዋቂ ሰዎች እና አምባሳደሮች እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እንደሚገኙ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የላከው መግለጫ ያመለክታል።

የሁለቱ ምክር ቤቶችን የጋራ ስብሰባም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሚያደርጉት ንግግር የሚከፈት ይሆናል።
በፕሬዚዳንቷ የመክፈቻ ንግግርም በ2013 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የሚያከናውናቸው ተግባራት ይፋ ይደረጋሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version