Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በህንድ በኮቪድ-19 ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ አለፈ

አዲስ አበባ፣መስከረም 23 ፣ 2013(ኤፍ.ቢ.ሲ)በህንድ በኮቪድ-19 ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 100 ሺህ ማለፉን የሀገሪቱ የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
በሀገሪቱ የተመዘገው የሞት ቁጥር በዓለም ላይ ከአሜሪካ እና ብራዚል በመቀጠል ህንድን ሦስተኛ ደረጃ እንድትዝ አድርጓታል።
በተለይም መስከረም ወር በሀገሪቱ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሞት ቁጥር መመዝገቡን ባለስልጣናቱ ጠቁመው÷ በአማካይ በየቀኑ 1 ሺህ 100 ህንዳውያን በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።
ይህም በሀገሪቱ በአጠቃላይ በቫይረሱ ከተያዙት 41 በመቶ የሚሆኑት እና በአጠቃላይ በቫይረሱ ከሞቱት 34 በመቶው የሚሆነው ቁጥር የተመዘገበው በመስከረም ወር ብቻ ነው ብለዋል።
ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ በወረርሽኙ ከሚሞቱት ከ 1 ሚሊየን በላይ ሰዎች መካከል 10 በመቶው የሚሆኑት በሕንድ ውስጥ የሚመዘገብ የሞት መጠን መሆኑን ጠቁመዋል።
ህንድ 6 ሚሊየን 504 ሺህ 916 ዜጎቿ በበሽታው መያዛቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።
ምንጭ፡-ቢቢሲ እና ዎርልዶ ሜትር
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
Exit mobile version