አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መቐለ ዩኒቨርስቲ ለ8 ምሁራን ሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታወቀ።
የዩኒቨርስቲው ቦርድ በዛሬው ዕለት ለ8ቱ ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረጉን አፅድቋል።
በዚህም መሰረት ዶክተር አፈወርቅ ሙሉጌታ ፣ ዶክተር ኢብራሂም ፍትዊ ፣ ዶክተር ክንፈ አብርሃ ፣ ዶክተር ምሩፅ ሃጎስ ፣ ዶክተር ገብረህይወት ታደሰ ፣ ዶክተር መሀመድ ኢስማኤል ፣ ዶክተር አለማየሁ ባይራይ እና ዶክተር ሀፍቱ በርሄ ሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል።

