አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ከሚገኘው የዓለም ባንክ ጽህፈት ቤት አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
ውይይቱ ያተኮረው ነባር የጋራ ፕሮግራሞችን በማጠናከር እና ተጨማሪ የትብብር ዘርፎችን በመዳሰስ ላይ ነበር ተብሏል፡፡
የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ መንግስት ተግባራዊ ለሚደረጉ የማሻሻያ ፕሮግራሞች ባንኩ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በኢትዮጵያ የባንኩ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን በበኩላቸው ከመንግስት ጋር ይበልጥ ውጤታማ የሆነ አጋርነት ለመመሥረት እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

