Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአርመኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከአዛርባጃን ጋር የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአርመኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሽንያን ከአዛርባጃን ጋር በናጎሮኖ ካራባህ ጋር በተያያዘ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃገራቸው ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አርመኒያ ተመሳሳዩን ለመፈጸም ፈቃደኛ ከሆነች ልዩነቶችን በመፍታት መግባባት ላይ ለመድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡

ግጭቶች በጋራ ስምምነት ላይ ተመስርተው መፈታት አለባቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዘርባጃን ፈቃደኛ ከሆነች ናጎሮኖ ካራባህም ሆነች አርመኒያ ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በናጎሮኖ ካራባህ በአርመኒያ እና አዘርባጃን መካከል በተፈጠረ ግጭት ወደ 300 የሚጠጉ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ይነገራል፡፡

የግጭታቸው መነሻ የሆነው ናጎሮኖ ካራባህ ከፈረንጆቹ 1994 ጀምሮ በአርመኒያ በሚደገፉ አርመናውያን ቁጥጥር ስር መሆኑ ይነገራል፡፡

ሁለቱ ሃገራት ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የአሜሪካ፣ ሩሲያ እና ፈረንሳይ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች አፋጣኝ የተኩስ አቁም ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን

Exit mobile version