Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ለሁሉም ትምህርት ቤቶች በነፃ ይሰጣል- ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 27 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር መደበኛ ትምህርት ለመጀመር አስፈላጊ ዝግጅቶችን እያጠናቀቀ እና በትምህርት ቤቶች አስፈላጊ ግብአቶችን ለማሟላት ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

በዚህም ሚኒስቴሩ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ለሁሉም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በነፃ እንደሚሰጥ የሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ሃረጓ ማሞ ተናግረዋል።

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛውም አዲስ አበባ እና ሀዋሳን ማዕከል በማድረግ ለክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች እንደሚከፋፈሉ ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል።

የዓለም የጤና ድርጅት መስፈርቶችን የሚያሟሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎችም ሀገር ውስጥ ካሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግዢ የመፈፀም ስራ እየተከናወነ እና በቅርቡ ወደ ትምህርት ቤቶች የማድረስ ስራ እንደሚሰራ ተገልጿል።

ለተማሪዎች የሚከፋፈለው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በተደጋጋሚ ታጥቦ ዳግም አግልግሎት መስጠት የሚችል መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version