Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን በየደረጃው ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው

አዲስ አበባ ፣መስከረም 27 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች በየደረጃው ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ የሚያስችል ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በቅርቡ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በየተራ ተማሪዎቻቸውን እንደሚቀበሉ የጠቆመው ሚኒስቴሩ÷ በሀገሪቱ ሁሉም ክልል የሚገኙ ተማሪዎችም በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለማምራት ዝግጅት ማድረግ አለባቸው ብሏል።

ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ 44 ዩኒቨርሲቲዎች በተደረገ ግምገማ አብዛኛዎቹ ኮሮናን በመከላከል የመማር ማስተማሩን ሂደት ማከናወን በሚችሉበት ደረጃ ላይ እንደሚገኙም ገልጿል።

የቀሩት ጥቂት ዩኒቨርሲቲዎችም በቀጣይ ሳምንት ዝግጅታቸውን እንዲያጠናቅቁ አቅጣጫ መሰጠቱ ተጠቁሟል።

የጤና ፕሮቶኮልና የሰላም ሁኔታውን የሚያስጠብቅ መመሪያም ተዘጋጅቷል ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም በአመቱ ከክህሎትና እውቀት በተጨማሪ የስብእና ግንባታ ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችን በስርአተ ትምህርቱ ይካተታል ተብሏል።

በኃይለኢየሱስ ስዩም

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version